የምንናመነው

የእምነት መግለጫ

አምልኮአችንን፣ ደቀመዝሙርነታችንን እና ተልዕኮአችንን የሚመሩ የእምነት መሠረቶች።

I. መጽሐፍ ቅዱስ

ቅዱስ መጽሐፍ በመንፈስ ቅዱስ ተነስተው በሰዎች የተጻፈ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው የገለጠበት መገለጥ ነው። እርሱ ፍጹም የመለኮታዊ ትምህርት ሀብት ነው። ደራሲው እግዚአብሔር ነው፣ ዓላማውም ድነት ነው፣ ይዘቱም እውነት ነው። ስለዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ሁሉ ፍጹም እውነትና የታመነ ነው።

II. እግዚአብሔር

አንድ ብቻ ሕያውና እውነተኛ እግዚአብሔር አለ። እርሱ ፈጣሪ፣ አዳኝ፣ ጠባቂና የዓለም ገዢ ነው። በቅድስናና በፍጹምነት የማይመጣጠን ነው። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በሚለው ሦስትነት ራሱን ይገልጣል፤ በባህርይ አንድ፣ በአካል ሦስት ናቸው።

a. እግዚአብሔር አብ

እግዚአብሔር አብ በፍጹም ጥበብ፣ ፍቅርና ኃይል ፍጥረቱን ሁሉ ይጠብቃል፣ ይመራል፣ ይገዛል። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት የእግዚአብሔር ልጆች ለሚሆኑ በእውነት አባት ነው።

b. እግዚአብሔር ወልድ

ክርስቶስ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም ተወለደ። ያለ ኃጢአት ፍጹም ሰው ሆኖ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጸመ። በመስቀል ላይ በሞቱ ለሰው ኃጢአት የማዳን መንገድ አዘጋጀ፤ ከሙታንም ተነሣ፣ ወደ ሰማይም አረገ፣ በአብ ቀኝም ተቀመጠ።

c. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ ፍጹም መለኮታዊ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ቅዱሳን ጽሑፎችን እንዲጻፉ አነሳሳ፣ እውነትን እንድንረዳ ያበራል፣ ክርስቶስን ያከብራል፣ ሰውን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሳል። በአማኞች ውስጥ ይኖራል፣ ያጽናናል፣ ያበረታታል፣ ለአገልግሎትም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጣል።

III. ሰው

ሰው በእግዚአብሔር ልዩ ፍጥረት ሲሆን በእግዚአብሔር ምስል ተፈጥሯል። እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። በመጀመሪያ ሰው ከኃጢአት ነጻ ነበር፣ ነገር ግን በነፃ ፈቃዱ እግዚአብሔርን በመቃወም ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ። ስለዚህ የሰው ሁሉ ክብር በእግዚአብሔር ምስል መፈጠሩና ክርስቶስ ስለ ሰው መሞቱ ውስጥ ይታያል።

IV. ድነት

ድነት የሰውን ሙሉ ሕይወት የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታና አዳኝ ለሚቀበሉ ሁሉ በነፃ ተሰጥቷል። በሰው ስራ ሳይሆን በክርስቶስ ደምና በግል እምነት ብቻ ይገኛል። ድነት ዳግም መወለድን፣ መጽደቅን፣ መቀደስን እና መክበርን ያካትታል (ዮሐ 1፥12-13፤ ሮሜ 8፥30፤ 1ኛ ተሰ 5፥23)።

V. ቤተክርስቲያን

የቤተክርስቲያን መሰረቷና ራሷ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ኤፌ 5፥23፤ ቆላ 1፥18፤ ሮሜ 12፥4፤ ማቴ 16፥15-18)። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለሰው ልጆች ድነት በከፈለው ዋጋ ከኃጢአታቸው ታጥበውና ከዓለም ርኩሰት ተለይተው፣ እርሱን ለማምለክና ለማገልገል የተጠሩ የአማኞች ህብረት ቤተክርስቲያን ተብላ እንደምትጠራ እናምናለን (1ኛ ጴጥ 2፥9)።

ቤተክርስቲያን የተገለጠችበት መንገድ፦

  • ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን (Universal Church) — የማትታየዋ (ማቴ 16፥18፤ ኤፌ 1፥22-23፤ ቆላ 1፥18)
  • አጥቢያ ቤተክርስቲያን (Local Church) — የምትታየዋ (ፊሊ 1፥1፤ 1ኛ ተሰ 1፥1፤ 1ኛ ቆሮ 1፥2፤ ቆላ 1፥2፤ 3፥15)

ዓላማዋና ተግባሯ፦

  • የወንጌል ተልዕኮን መፈፀም (ሐዋ 1፥8፤ ማቴ 28፥19-20)
  • ደቀመዛሙርቶችን ማፍራት (ማቴ 28፥19-20፤ ኤፌ 4፥11-16)
  • በእውነትና በመንፈስ እግዚአብሔርን ማምለክ (ዮሐ 4፥24፤ ሮሜ 12፥1)
  • ከቅዱሳን ጋር ህብረት ማድረግ (መዝ 133፥1-3፤ ዕብ 10፥24-25)

VI. የዘመን ፍፃሜና የሙታን ትንሳኤ

እናምናለን፦

  • እግዚአብሔር በራሱ መንገድ በወሰነው ጊዜ ዓለምን ወደ ፍፃሜው እንደሚያመጣ (ራዕ 20፥11፤ 21፥1)
  • እንደ ተስፋ ቃሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገልጦ ወደዚህ ዓለም እንደሚመጣ (ማቴ 16፥27፤ 25፥31-46)
  • ክርስቶስ በሰዎች ሁሉ ላይ በጽድቅ እንደሚፈርድ (ዮሐ 5፥27-29)
  • የሞቱ ሁሉ እንደሚነሱ (ራዕ 20፥12-13)፣ በሕይወት ያሉትም በትንሳኤ አካል ተለውጠው ክርስቶስን በደመና እንደሚቀበሉት (1ኛ ቆሮ 15፥51-52፤ 1ኛ ተሰ 4፥13-18)
  • የተፈረደባቸው ኃጢአን ለዘላለም ወደሚቃጠሉበት ስፍራ እንደሚጣሉ (ራዕ 20፥15፤ ማቴ 25፥31-46)
  • ጻድቃን ግን ከጌታ ኢየሱስ ጋር በክብር በተነሳው አካል ለዘላለም በመንግስቱ እንደሚኖሩ (ማቴ 25፥46)